በሆሞሻ ወረዳ በጉሚ-አቡሽ ቀበሌ በዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮጀክት /RLLP/SLMP/የበጀት

በሆሞሻ ወረዳ በጉሚ-አቡሽ ቀበሌ በዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮጀክት /RLLP/SLMP/የበጀት ድጋፍ ለ832 አርሶ አደሮች ቋሚ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ ፡፡******************************************************************************************
በቀን 30-1.2133ዓ.ም
በሆሞሻ ወረዳ በጉሙ-አቡሽ ቀበሌ በዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ለ832 አርሶ አደሮች ቋሚ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ከክልል ፣ከዞን፣ከወረዳ ፣የቀበሌ አመራሮች እና ማህበረሰቡ በተገኙበት ተሰጥቷል፡፡
በስነስራዓቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳው የአካባቢ ጥበቃ መሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አብዱልመጅድ መሃመድ ወረዳው በህገ-ምግሰቱ እና በአዋጁ በተሰጠው ሃላፊነት መሰረት አርሶ አደሩን የመሬት ባለቤትነት ማድረግ ሲሆን አገራችን ካለችበት ድህነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ተርታ ማሰለፍ እንድትችል አርሶ አደሩን የመሬት ባለቤት ማድረግ ወሳኝ ተግባር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በዛሬው ዕለት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የወሰዳችሁ የቀበሌአችን አርሶ አደሮች የመሬት ባለቤትነት መሆን ብቻ ብልጽግናን የማያረጋግጥ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ብልጽግናን ማረጋገጥ የምንችለው በእጃችን ያለው መሬት በመስኖም ሆነ በዝናብ በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ ማልማት ስንችል ፤ መሬታችንን ሙሉ በሙሉ በዘር ሲሸፈን እና መሬታችንን በአግባቡ በማልማት ምርትና ምርታማነት በማሳደግ እንደሆነ አሳስበዋል፡፡
እንዲሁም በፕሮግራሙ ላይ የክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና የቢሮው ተወካይ አቶ አህመድ ራህማ በወረዳው ለአርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መስጠት የተቀዋሙ ዋና ተግባር እንደሆነ እንደሆነ በመግለጽ ስራው በዚህ ቀበሌ ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን ሁሉም የወረዳው አርሶ አደሮች እንዲያገኙ ለማድረግ እንደሚሰራ እና ድጋፉም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መልዕካታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በአጠቃላይ ስራው 834 የተለያዩ የይዞታ አይነቶች የመመዝገብ ስራ የተሰራ ሲሆን ከዚህም ውስጥ በግለሰብ የተያዘ 795 ማሳ ከህም ውስጥ የባል አባወራ ባለይዞታ 6 ማሳ ፣የግል እማወራ ይዞታ 88 ማሳ፣ በጋራ በባል እና በሚስት የተያዘ 6671 ማሳ ፣በተቋም የጠያዘ 13 ማሳ ፣የወል ይዞታ 24 ማሳ ፣የማህበር 2ይዞታዎች የተለኩ እና የተመዘገቡ ናቸው ፡፡ ከተለኩ እና ከመዝገቡ84 ማሳዎች ውስጥ 832 ማሳዎች ችግር የሌለባቸው በመሆኑ ወደ ባህረ መዝገብ በማስፈር የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እንደተሰጠ የወረዳው የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ክንዴ ጎሹ ገልጸዋል፡፡
በሆሞሻ ወረዳ በጉሚ-አቡሽ ቀበሌ በዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮጀክት /RLLP/SLMP/የበጀት ድጋፍ ለ832 አርሶ አደሮች ቋሚ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ ፡፡*

Ketemit Kasa, Guteta Birhanu and 17 others
4 Comments
Like

Comment