የቢሮው የማናጅመት አባላት የተቀናጀ የሙስና መከላከል ዕስትራቴጅክ

የቢሮው የማናጅመት አባላት የተቀናጀ የሙስና መከላከል ዕስትራቴጅክ የ5 ዕቅድ ለማቀድ ካወንስል በማቋቋም እና ሰራተኞች የሃብት ማስመዝግብ ስራ አከናወነ፡፡
 በቀን 17.3.2013 ዓ.ም
የቢሮው ኃላፊ የሆት የተከበሩ አቶ ገለታ ሓይሉ ለማናጅመት አባላት እንደገለጹት ቢሮው የተሰጠውን ተልዕኮ እና ያስቀመጠውን ራዕይ ለማሳካት እንቅፋት ከሚሆኑት ተግዳሮቶች መካከል አንዱ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ድርጊት (ሙስናና ብልሹ አሰራር) ነው፡፡ ስለሆነም ይህንን ተግዳሮት በብቃት ለመወጣት ከሚያስችሉት መሰረታዊ ጉዳዮች አንዱ ለሙስናና ብልሹ አሰራር ተጋላጭ አሰራሮችን መለየትና ይህንንም ለማክስም የተቀናጀ የሙስና መከላከል ስትራቴጅ በመዘርጋት ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልግል በማለት ለማናጅመት አባላት አስረድተዋል
ከዚህ በተጨማሪ የቢሮው የስነምግባር እና ጸረ-ሙስና መኮነን የሆኑት ወ/ሮ መሰረት አበበ እንደገለጹት የስትራቴጂዉ ዕቅድ ዓላማ በገጠር መሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመት በአገልግሎት አሰጣጥ አፈጻጸም ወቅት ሙስና ከመከሰቱ ወይም ከመፈጠሩ በፊት ወይም ተፈጥሮም ከሆነ መጠነ-ሰፊ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ሊደርስ የሚችል ጉዳትን ሙሉ ለሙሉ እንዳይደርስ ወይም የጉዳት መጠኑ ዝቅተኛ እንዲሆን በማድረግ ሙስና ሊያስከትል የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ኪሳራዎችን በመቀነስ የችግሩን ምንጭ ለማድረቅ የካወንስሉ መቋቋም አስፈላጊነት አስረድተዋል፡፡
የቢሮው የማናጅመት አባላትም የሙስናና ብልሹ አሰራር መክሰም የቢሮውን ራዕይ እና ተልዕኮውን ለማሳካት አይነተኛ ድርሻ እንዳለው በማመን የሙስና ምንነትና የሚያስከትለው ጉዳት፣ የሙስና መከላከል ስትራቴጂ አጠቃላይ አቅጣጫ፣ ሕጋዊ ማዕቀፎች፣ የሙስና ስጋት አካባቢዎችና መገለጫዎች፣ የሙስና መዋጊያ አጠቃላይ ስልቶች እና የሙስና መከላከል ካውንስል አደረጃጃትና ተግባርና ኃለፊነቶችን በማከተት ይህን የተቀናጀ የሙስና መከላከል ስትራቴጂ ዕቅድ እንዲታቀድ ለመድረግ ተገቢ እንደሆነ በማመን ካውንስሉን አቋቁመዋል፡፡
በመጨረሻም የማናጅመቱ አባላት የሃብት መስመዝግብ ስራ የገመገሙ ሲሆን በተቋሙ የሚገኙ ሰራተኞች ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ቅጽ የወሰዱ ሲሆን አብዛኛዎቹ ቅጹን ሞልተው የመለሱ ሲሆን ቀሪዎቹም ያልመለሱ እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን ለዚህም ምክንያት ሰራተኞቹ ለመስክ ስራ ባለመኖራቸው እንደሆነ ሲሆን በአጭር ጊዜ ከመስክ ሲመለሱ በተሰጠው ጊዜ ቶሎ ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ አሳስበዋል፡፡