በባምባሲ ወረዳ መንደር 5ዐ ቀበሌ በGIZ ኘሮጀክት /በጂ አይ ዜድ / የበጀት ድጋፍ ለ225 አርሶ አደሮች ቋሚ የይዞታ ማረጋጫ ደብተር ተሰጠ፡
*******************************************************************************************************************************************************
በቀን 18-3.2133ዓ.ም
በባምባሲ ወረዳ በመንደር 50 ቀበሌ በጂ አይዜድ /G-IZD/ ፕሮጀክት የበጀት ድጋፍ ለ225አርሶ አደሮች ቋሚ የይዞታ ማረጋገጫ ደብርተር ከክልል ፣ከዞን፣ከወረዳ ፣የቀበሌ አመራሮች እና ማህበረሰቡ በተገኙበት ተሰጥቷል፡፡
በስነስራዓቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳው የአካባቢ ጥበቃ መሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሃሩን አብዱልቃድር እንዳሉት ከዚህ በፊት መንግስት በወረዳው የተለያዩ መንግስታዊ ያሆኑ ድርጅቶችን ከህዝቡ ጐን እንዲሰለፉ በማድረግ ምላሽ ያልተሰጣቸውን የህዝብ ጥያቄዎችን መሠረት ለማድረግ እና የዕድገት ትራንስፎርሜሸን ዕቅድ ለማሳካት በነደፈው ቃጣይነት ያለወ ዕቅድ የዘርፉን ሥራዎች በማቃናጀትና በማደራጀት እንዲመራ በማድረግ መንግስት በፈጠረው ምቹ ሁኔታ ከፖሮጀክቶች ጋር በመተባበር የአርሶአደሩን የይዞታ መሬታቸውን በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ አገልግሎት ለማዋል ሲባል ህጋዊ ስርዓት ተከትሎ ማንኛውም የገጠር መሬት ለባለይዞታዎች በህጋዊ መንገድ ባለይዞታዎቹ መሬታቸውን በህጋዊ መንገድ ለማገኘት የቀጣይ በይዞታ መሬቱ ላይ የመጠቀም መብትና ዋስትና እንዲያገኝ ሲባል የክልሉ መንግስት አገራዊ አቅጣጨዎችን ተከትሎ ስልታዊ የገጠር መሬት ይዞታን በዘመናዊ መሥሪያ ከርታና GPS በመጠቀም የእያንዳንዱ የባለይዞታዎች ማሣ የመሬት መዝገባና ቅየሣ በማድረግ የባለይዞታዎችን ማሳ በተመዘገበላቸውና በተላከላቸው ይዞታቸው በትክክለኛ መረጃ ላይ በመቆም ለእያንዳንዱ ባለይዞታ በተመዘገበላቸው እና በተላከላቸው የመሬት ስፋትና መጠን መማላት የሚገኝባቸው መረጃዎችን የተማሉ መሆናቸውን በማረጋጥ የባለይዞታዋች የይዞታ መረጋገጨ ደብተር እና የማሣ ከርታ አርሶ አደሩን የመሬት ባለቤት ማድረግ ወሳኝ ተግባር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በአጠቃላይ ስራው በቀበሌው ላይ 1‚633 ማሳዎች የተለኩ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የተዘጋጀላቸው ለ133 አባወራ እና እማወራ 817 ማሳዎች ለ53 እማወራዎች 235 ማሳዎች ለ28 አባወራዎች 82 ማሳዎች እና የወል 5 የተቋማት 3 ማሣዎች ብዛት 11 በድምሩ 115ዐ/አንድ ሺህ አንድ መቶ አምሳ/ ማሳዎችን ልኬትና ምዝገባ በማከናወን ለ225 አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ለመስጠት ተችሏል፡፡