በአሶሳ ወረዳ በባሮ እና ያምፓሲዚም ቀበሌ በሪይላ ፕሮጀክት /REILA/ እና /RLLP/SLMP/ ፕሮጀከት

በአሶሳ ወረዳ በባሮ እና ያምፓሲዚም ቀበሌ በሪይላ ፕሮጀክት /REILA/ እና /RLLP/SLMP/ ፕሮጀከት የበጀት ድጋፍ ለ679 አርሶ አደሮች ቋሚ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ፡፡
በቀን 9-4.213ዓ.ም
በአሶሳ ወረዳ በበባሮ እና በአፋሲዝም ቀበሌ በሪይላ /REILA/ እና /RLLP/SLMP/ ፕሮጀክት የበጀት ድጋፍ ለባሮ አርሶ አደሮች 509 እና ለያምባሲዝም 170 አርሶ አደሮች ቋሚ የይዞታ ማረጋገጫ ደብትር የተሰጠ ሲሆን በአጠቃላይ 679 አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ደብርተር ከክልል ፣ከዞን፣ከወረዳ ፣የቀበሌ አመራሮች እና ማህበረሰቡ በተገኙበት ተሰጥቷል፡፡
በወረዳዉ እስካሁን ቅየሳ የተደረገላቸዉ በግልና በጋራ 10,568 ሲሆኑ፣ በ2012 በጀት ዓመት 9,514አርሶ ማሳዎች ቋሚ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የተሰጠ መሆኑ ተብራርቷል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኑ ሰዓት በባሮ ቀበሌ የተለኩ የአርሶ አደር ማሳዎች ብዛት 1,504 አርሶ አደሮች ሲሆን፣ከእነኚህ ዉስጥ 1,259 ያህሉ ምንም ዓይነት ችግር የሌለባቸዉና ባህር መዝገብ ላይ የሚሰፍሩ መሆኑን ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም ለ390 ባልና ሚስት 1‚113 ማሳዎች፣ለ44 አባወራዎች 58 ማሳዎች ፣ለ64 እማወራዎች 77 ማሳዎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ የይዞታ ዓይነቶች ሲሆኑ በያምባሲዝም ቀበሌ የተለኩ የአርሶ አደር ማሳዎች ብዛት 659 ሲሆን ፣ከእነኚህ ዉስጥ 495 ማሳዎች ያህሉ ምንም ዓይነት ችግር የሌለባቸዉና ባህር መዝገብ ላይ የሚሰፍሩ መሆኑን ተመላክቷል፡፡ በተጨማሪም ለ110 ባልና ሚስት 312 ማሳዎች፣ለ23 አባወራ 47 ማሳዎች ፣ለ 9 እማወራ 13 ማሳዎች እና 28 ሌሎች ልዩ ልዩ የይዞታ ዓይነቶች መሆናቸዉን በእለቱ ከቀረበዉ ሪፖርት ላይ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ በሁለቱም ቀበሌዎች የተሻለ የስራ አንቅስቃሴ ላሳዩ ለገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ኮሚቴዎች የእዉቅና ሰርትፍኬት ተሰጥቷል፡፡
በመጨረሻም በአርሶ አደሮች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ያነሱ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎች ምልሽ በመስጠት እና ቋሚ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በመስጠት ስነስራዓቱ ተጠናቋል፡