ስልጣንና ተግባራት

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የክልሉን የአስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማደራጀት ባዉጣዉ አዋጅ ቁጥር 197/2015 ዓ/ም መሰረት ቢሮዉ የሚከተሉትን ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

  1. ለመሬት ተጠቃሚ አርሶ አደሮች ወይም ድርጅቶች የይዞታ የመጠቀሚያ መሬት ትክክለኛ ስፋት በመወሰን ይለካል ደብተር ለመስጠት የአሰራር መንዋል በማዘጋጀት አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል
  2. ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመተባበር የክልሉን የመሬት ዓይነትና መጠን አጥንቶና መዝግቦ ይይዛል፤ያስተዳድራል፤አጠቃቀሙን ይወስናል፤ይቆጣጠራል፤ ዉጤታማነቱን ይገመግማል እንደ አስፈላጊነቱ መረጃዉን ለተጠቃሚዎች ይሰጣል
  3. መሬት በተለያዩ ምክንያቶች እንዳይጎሳቆል ወይም ምርታማነቱን እንዳያጣና ከጥቅም ዉጭ እንዳይሆን የመሬት ተጠቃሚዎች በይዞታቸዉ ላይ የተለያዩ እንክብካቤዎች እንዲያደርጉ ትምህርት ይሰጣል፤የማትጊያ ዘዴዎችን ይቀይሳል፤ግዴታቸዉን በማይወጡ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዳል፤
  4. በመሬት የመጠቀም መብት የተሰጣቸዉ ግለሰቦች/ድርጅቶች የያዙትን መሬት የመጠቀም መብት በዉርስ/በስጦታ/በኪራይ የሚያስተላልፉበትን እና ሌሎች መሬትን ለማስተዳደር የሚወጡ ደንቦችና መመሪያዎችን ይቀርጻል ሲፈቀድም ያስፈጽማል
  5. የግል ባለሀብቶች በመሬት ላይ የልማት ስራ ከመጀመራቸዉ በፍት የአጠቃቀም ዕቅዳቸዉን እየገመገማ ያጸድቃል፤በዕቅዱ መሰረት ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል
  6. የክልሉን የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር መረጃዎችን ለማደራጀት ስርዓት ይዘረጋል፤ክልላዊ የመረጃ ቋት ይመሰርታል፤መረጃዎችን ያሰባስባል፤ትንተና እያካሄደ ወቅታዊ ማስተካከያዎችን ያደርጋል፤በአካባቢና በተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ ፍላጎት ላላቸዉ ተጠቃሚዎች ዝግጁ ያደርጋል ያሰራጫል፤
  7. የክልል የልማት ስትራቴጂዎችና  ፖሊሲዎች   ዘላቂ   የመሬት   አጠቃቀምን   መሰረት አድርገዉ እንዲተገበሩ ክልል አቀፍ መሪ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ያዘጋጃል፤
  8. በክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም በሚመለከቱ ጉዳዮች አግባብ ላላቸው አካላት የቴክኒክ ምክርና ድጋፍ ይሰጣል፤
  9. የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም የሕግ ማዕቀፎችን ያዘጋጃል፣ የሚመለከተው አካል ሲያፀድቅም በበላይነት ይተገብራል፣ ይደግፋል፣ ይቆጣጠራል፣ ዝርዝር የአሠራር ሂደቶችን ማንዋልችን እንዲሁም ላሎች የሥነ-ምዳር መረጃ ማሰባሰቢያና ማሰራጫ ቅፃቅጾችን በማዘጋጀት ያሰራጫሌ፤
  10. ለህዝብ ጥቅም ሲባል ይዞታውን እንዲለቅ ለሚደረግ የገጠር መሬት ባለይዞታ ተመጣጣኝ ካሣ ማግኘት እንዲችል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ይሰራል፣ አፈጽጸሙንም ይከታተላል፣ ድጋፍ ያደርጋል፤
  11. ከገጠር መሬት የይዞታና የመጠቀም መብት ጋር ተያይዞ የሚነሱ አቤቱታዎች፣ አለመግባባቶችና ቅሬታዎችን በማጣራት ተገቢውን አስተዳደራዊ ምላሽ ይሰጣል፤
  12. አዲስ የይዞታና የመጠቀም መብት  በመለየት  በህጉ  መሠረት  የመሬት  አቅርቦት ያመቻቻል፣ ለሚመለከተው አካል አቅርቦ ያስፀድቃል፣ አስፈሊጊውን ውል እንዲይዙ ያደርጋል፣ ድጋፍ ያደርጋል፣ ይቆጣጠራል፣ ግዳታቸውን በማይወጡ ተጠቃሚዎች/ ባለይዞታዎች ላይ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዳል፤
  13. በገጠር መሬት ላይ ለሚሰማሩ አልሚ የግል ባለሃብቶች በሕጉ መሠረት የመሬት አቅርቦት ያመቻቻል፣ ለሚመለከተው አካል አቅርቦ ያስፀድቃል፣ አስፈሊጊውን ውል እንዱይዙ ያደርጋል፣ የመጠቀም መብት ያስከብራል፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን አፈጻጸማቸዉን በመከታተል ድግፍ ያደርጋል፤ይቆጣጠራል፤ግዴታቸዉን በማይወጡ ተጠቃሚዎች/ባለይዞታዎች ላይ አስፈላጊዉን አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዳል፡፡
  14. በግል፣ በጋራ፣ በወልና በመንግስት የገጠር መሬት ይዞታዎች ላይ መረጃ በማሰባሰብ፣ በማጠናከርና በመተንተን ጥራት ያለውና ወቅታዊ መረጃ ለተጠቃሚው ያደርሳል፣ ክልላዊ የገጠር መሬት የካዳስተር እና ሌሎች መሬጃዎች ቋት በመፍጠር ለተገልጋዩ እንዲደርሱ ያደርጋል፣ የማሳን የመረጃ ለውጥ በየጊዜው በመከታተል በመመዝገብ ወቅታዊ ያደርጋል፤
  15. የገጠር መሬት ምዝገባ ሥርዓት ይዘረጋል፣ይተገብራል፣አፈጻጸሙንም ይደግፋል፣ በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም የሚከናወኑ ሥራዎች በበላይነት ያቅዳል ይፈፅማል፣ ይከታተላል፣ሪፖርቱንም ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ያደርሳል፤
  16. ከአከባቢያዊ፣ ከኢኮኖሚያዊና ከማህበራዊ አገልግሎት አንፃር ጠቄሜታቸው የጎላ የገጠር መሬቶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጥናት በመለየት የይዞታና የመጠቀም መብት ያረጋግጣል፤
  17. የክልል ልማትና ዕድገት የሚያስፈልጉ የገጠር መሬት የካዳስተር ቅየሳ፣የካርታና ሌሎች የሥነ ምዳር መረጃ ያሰባስባል፣ ይተነትናል፣ ጥናት ያደርጋል፣ወቅታዊ ማስተካከያዎችን እያደረገ ተግባራዊ ያደርጋል፤
  18. የገጠር መሬትን ለተሻለ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ተጠቃሚነትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ እንዲቻል በተለያዩ ደረጃ የገጠር መሬት አጠቃቀም እቅድ   ያዘጋጃል፣ አተገባበሩን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣   በሚወጣው   የአጠቃቀም   እቅድ   መሠረት ግዴታቸውን በማይወጡ ተጠቃሚዎች ባለይዞታዎች   ላይ   አስፈላጊውን   አስተዲደራዊ እርምጃ ይወስዲል፤
  19. የአባላትን ፍላጎት መሰረት በማድረግ የሴቶችንና ወጣቶችን ተሳታፊነትንና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የተለያዩ ማህበራትን ያደራጃል፣ የአባላት ቁጥር በየጊዜው እንዲጨምር ትምህርትና ቅስቀሳ ያደርጋል፣ አቅም ይገነባል፣ ይከታተላል፤ ያጠናክራል፡፡
  20. ዓለም አቀፍ የህብረት ሥራ መርሆችን መሰረት በማድረግ የተደራጁ ማህበራት  በክልል ብሎም በአገር ዓቀፍ የኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተሳትፈፎአቸው እንዱያድግ አደረጃጀታቸውን፣  አሰራራቸውን  እና   አገልግሎት   አሰጣጣቸውን   በማዘመን ቀጣይነታቸውን የማረጋገጥ ሥራ ይሠራል፡፡
  21. በክልሉ ውስጥ የአባላትን ፍላጎት መሰረት ያደረገ የኅብረት ስራ ማህበራትን የማደራጀት፣ አቅም የመገንባት እና የማጠናከር ሥራ ይሰራል፤ የህብረተሰቡን የቁጠባ በህል ከማሳደግ አንፃር መደበኛና ወለድ አልባ የገጠር ፋይናንስ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበራትን እንዲደረጁ ያደርጋል፤ ይከታተላል፤ ያጠናክራል፡፡
  22. በህግ አግባብ የተደራጁ ማህበራትን ይመዘግባል፤ ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ሰርቴፊኬት ይሰጣል፤ ይሰርዛል፤ የኢንስፔክሽን ሥራ በመስራት የአሰራር ክፍተቶች ካሉ ወቅታዊ ማስተካከያ ያደርጋል፡፡
  23. የፖሊሲ ሃሳቦች ያመነጫል፤ የምርምር ተግባራትን ያከናውናል፣  ስትራቴጅዎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በክልሉ ውስጥ ይፈፅማል፣ ይተገብራል፡፡
  24. የኅብረት ሥራ ማህበራትን ልጠቅሙ የሚችሉ እና በአባላት ተሳትፎ የሚሰሩ የልማት ፕሮጀክቶች እንዱዘጋጁ በማድረግ የአፈፃፀም ስትራቴጂ እና ቅደም ተከተል እንዱወጣ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር በተግባር ላይ መዋላቸውን ይገመግማል፤ይከታተላል፡፡
  25. የኅብረት ሥራ ማህበራት የሂሳብ አያያዝ ውስጥ የቁጥጥር ስርዓት እንዱጠናከር ሂሳብ የማስተካከል አገልግሎት  ሙያዊ  እገዛ  በመስጠት  የገንዘብ  እና  የንብረት  ብክነትን ይከልሳል፤ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ ተከታትሎ ወቅታዊ የሂሳብ ምርመራ ያደርጋል፤
  26. በማህበራት ሀብትና ንብረት ላይ ጥፋት ከመድረሱ አስቀድሞ በሚያደርጋቸው የሂሳብ ምርምራ ውጤት መሰረት የማስመለስ  ጥረት  ያደርጋል፤ተገቢው  ህጋዊ  እርምጃ እንዱወሰድ ያደርጋል፤ በክልሉ ውስጥ በየደረጃው ያሉ የኅብረት ስራ ማህበራትም ውክልና ሲሰጡትም የህግ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፤
  27. በክልሉ ውስጥ  ያሉ  የኅብረት  ሥራ  ማህበራት  የብቃት  ደረጃ   ማረጋጋጫ   እውቅና አሰጣጥና ምዘና በመስራት የደረጃ ማረጋገጫ ዕውቅና ይሰጣል፤
  28. ዘርፉ የሚጠይቀውን የሰለጠነ የሰው ኃይል በትምህርት ዝግጅትና በሙያ ያበቃል፣የአጭር እና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎች እንዱያገኙ ያመቻቻል ከሚመለከታቸው የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ጋርም በቅንጅት ይሠራል፡
  29. ኅብረት ሥራ ማህበራት በነፃ ገበያ ተወዲዲሪና ተጠቃሚ እንዱሆኑ እና የክልሉ ኢኮኖሚ ዕድገትም የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዱያበረክቱ ወቅታዊና አስፈሊጊ የገበያ መረጃዎች እንዲያገኙ ያድርጋል፡፡
  30. የክልሉን የመሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራትና ዩኔኖችን መረጃዎችን ለማደራጀት ሥርዓት ይዘረጋል፤ ክልላዊ የመረጃ ቋት ይመሰርታል፤መረጃዎችን ያሰባስባል፤ትንተና እያካሄደ ወቅታዊ ማስተካከያዎችን ያደርጋል
  31. በገጠር የተደራጁ ዩዬኒኖችና መሰረታዊ የህብረት ሥራ  ማህበራት  የተለያዩ  የግብርና ምርቶችን ከህገ-ወጥ ደለሎች በመከላከል ምርቱን በተሻለ ዋጋ በመሸጥ ቀጥተኛ ተጠቃሚ እንዱሆን ያደርጋል፣
  32. በከተማም ሆነ በገጠር የተደራጁ ዬኒኖችና መሰረታዊ የህብረት ሥራ ማህበራት የፍጆታ ዕቃዎችን፣ የኢንደስትሪ ውጤቶችን፣ የግንባታ ዕቃዎችን እንዱሁም የአባላትን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ለሎች ሸቀጣ ሸቀጦችን የአባላትና የአካባቢው ሸማች ማህበረሰብ እንዲያቀርቡ አስፈሊጊውን ድጋፍ ያደርጋል፣
  33. የተደራጁ ዩኒዬኖችና መሰረታዊ ማህበራት የግብርና ምርት ማሳደጊያ ቴክኖልጂዎችን (ፀረ- ተባይ፣ ፀረ-አረም፣ የሰብል ተባይ መከሊከያ ከረጢቶች እና ልዩ ልዩ የአትክልት ዘሮችን ለአባላትና ለአርሶ አደሩ በተመጣጣኝ ዋጋ የጥራት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ያቀርባል፣ የተመረተውን የአትክልት ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ እንዲያቀርቡ እገዛ ያደርጋል፣
  34. ዩኒዬኖችና መሰረታዊ የህብረት ሥራ ማህበራት መጋዘን፣  የመሸጫ  ሱቅ፣  የምርት መሰብሰቢያና መረከቢያ ማዕከላት የተሟላ  እንዱሆን  እገዛ  ያደርጋል፣  ምርታቸው  ላይ እሴት  ለመጨመር  የሚያስችል  የአግሮ  ፕሮሰሲንግ   ኢንደስትሪዎችን   በስፋት እንዱያቋቁሙ በማድረግ ለክልሉ ስራ ፈላጊ ወጣቶች የሥራ ዕድል እንዱፈጠር ያደርጋል፣
  35. የህብረት ስራ ማህበራትን የግብይት ፋይናንስ  ችግር  ለመፍታት  የሚያስችል  የተለያዩ የብድር ፕሮፖዛሎችን በማዘጋጀት ብድር ያስፈቅዳል፣ ከአቻ ማህበራትና ከተለያዩ አበዳሪ ተቋማት ጋር የፋይናንስ ትስስር ይፈጥራል፣
  36. የኑሮ ውድነትን ለመከላከል የሸማች ማህበራት የፍጆታ ዕቃዎች አቅርቦት የሚውል የተዘዋዋሪ ፈንድ ከሚመለከታቸው አካላት ያስፈቅዳል፣ ብድሩ ሲፈቀድም ገንዘቡ እንዳይባክን ይቆጣጠራል፣ ተከታትሎ የማስመለስ ሥራ ይሰራል፣
  37. ከግብርና ምርምርና ከግብርና ቢሮ ለምርጥ ዘርነት የሚለቀቁ የተለያዩ መስራች ዘሮችን የህብረት ስራ ማህበራት በክላስተር እርሻ እንዱያባዙ ያግዛል፣ ጥራቱ የተረጋገጠውን ዘር ይሰበስባል፣ ለአባላትና ለአባቢው አርሶ አደሮች በሚፈቀድላቸው የዋጋ ተመን መሰረት በወቅቱ እንዱሰራጭ ያደርጋል፣
  38. የኅብረት ስራ ማህበራት ተደራሽነት በገጠርም ሆነ በከተማ ለማስፋፋት እና ለማዳበር የሚያስችሉ ተከታታይ ትምህርትና ስልጠና በማዘጋጀት ለኅብረት ሥራ ማህበራት አባላት፣ ሠራተኞች እና ባለሙያዎች ስልጠና ይሰጣል፡፡
  39. በየደረጃው አስፈሊጊ የሆኑ አደረጃጀቶች እና የአሰራርር ሥርዓት ይዘረጋል፣ ያስተዳድል፤
  40. .አባላት በኅብረት ሥራ ማህበራቸው በኩል የምርት ማሳደጊያ ግብዓቶችን ብድር እንዱያገኙ የምርት ውጤቶችን እና አገልግሎታቸውን  እንዲያስተዋውቁ  የገበያ  ትስስር  በመፍጠር በተሻለ ዋጋ በመሸጥ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፤
  41. መሰረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበራትና ዩኒኖዬች የሚዋሄድበት እና በሚለያዩበት ወይም በሚፈርሱበት ጊዜ በህግ አግባብ እንዲፈጸም አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፡፡
  42. የህብረት ስራ ማህበራትን የሚመለከቱ ህጎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፡፡
  43. የራሱን ዕቅድ እና በጀት ያዘጋጃል፡፡ በጀቱ ሲፈቀድም ያስተዳድራል ስራ ላይ ያዉላል፡፡
  44. የተቋሙን የሰው ኃይል ያሟላል፣
  45. የኀብረት ስራ  ፌዴሬሽኖች፣  ዩኒዬኖችና  መሠረታዊ   ህብረት  ስራ  ማህበራት  በሚሰሩበት ሥራ  ወይንም  አገልግሎት  ውል  ይዋዉላል፣  ይከሳል፤ይከሰሳል፤
  46. ከአጎራባች ክልሎችና ከፌዴራል መንግሥት አካላት እንዱሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር/በመተባበር/ ይሰራል፣
  47. በኅብረት ሥራ ማህበራት ለሚደራጁ ሴቶችና ወጣቶች በቁጠባ እና ብድር አቅርቦት ድጋፍ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር የግብይት ትሥሥር ሥርዓት እንዲኖር ያደርጋል፡፡
  48. የግብርና ግብዓት አቅርቦትና ስርጭትን በኅብረት ስራ አማካኝነት ለህብረተሰቡ የምርት ግብዓት ማቅረብ፤ ማሰራጨት፤  ብድር  ማስመለስ፣  መቆጣጠር  እና  አፈፀፀሙንም ተከታትሎ በመገምገም የእርምት እርምጃዎችን ይወስዳል፤