የቢሮው ራዕይ ፤ ተልዕኮ እና እሴት
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የመሬት እና ህብረት ስራ ማደራጀት ቢሮ የራሱ የሆነ የቆመለት አላማ፤ ተልእኮ እና ራዕይ ያለው በአዋጅ ስልጣንና ተግባራት ተሰጥተውት የተቋቋመ ቢሮ ነው፡፡ በዛሬው እትማችንም የቢሮውን ተልዕኮ፤ ራዕይ ፤ እሴት እንዲሁም ስልጣንና ተግባራት እንደሚከተለው ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡
- ተልዕኮ /Mission/
ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር ስርዓት በመገንባት የህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀትና በማዘመን የክልሉ ህዝብ በዘለቀታዊነት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥ ማድረግ ነዉ፡፡
- ራዕይ /vision/
በ2022 በክልሉ ዘላቂ የመሬት አስተዳደር ስርዓት ተገንብተዉና አባላትን ተጠቃሚ ያደረጉ የህብረት ስራ ማህበራት ተፈጥረዉ ማየት፡፡
- እሴት /values/
- ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት መፍጠር
- ዉስን ሀብት ለህዝብ ጥቅም ማዋል
- ፍትሀዊ አገልግሎት መስጠት
- ለአካባቢያዊ ዕውቀት ክብር መስጠት
- የአርሶ አደሩ አስተማማኝ የመሬት ዋስትና ማረጋገጥ
- የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ
- የህብረት ስራ ማህበራትን ጤናማነት ማረጋገጥ
- ፍትሀዊ የአባላት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ
- የሥርዓተ-ፆታ ሥራዎችን የሥራ አካል ማድረግ፣