የፋይናንስ ክህሎት ማሳደጊያ ስልጠና (Financial Litracy) በኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን በተዘጋጁ የማስተማርያ መፅሀፎች/Toolkits/ ላይ አባላት እንዴት አድርገው ሀብት መፍጠር እንዳለባቸው፣ቁጠባቸውን እንዴት ማሳደግ እንዳለባቸው ፣ብድር እና እዳ አስተዳደር ፣ እንዴት የራሳቸውን የንግድ ድርጅት ማቋቋም እንዳለባቸው እና የአባላትን የፋይናስ ክህሎትና እውቀት ለማሳደግ ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ የገለጹት የክልል ኅብረት ስራ ፋይናንስ ባለሙያዎች ስልጠና መድረክ ላይ በአዳማ ከተማ ተገኝተው ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው ።
ክቡር ኮሚሽነሩ አክለውም የፋይናንስ ክህሎት የተለያዩ የፋይናንስ እውቀቶችን የመረዳት እና በብቃት የመጠቀም ችሎታ ሢሆን ይህም የግል የፋይናንስ አስተዳደር በጀት ማውጣትና ኢንቨስት ማድረግን የሚጨምር መሆኑን ጠቁመው ይህም የሃገራዊ ሪፎርማችን አንዱ አካል ነው ብለዋል።
የፋይናንስ ኅብረት ስራ ማህበራት የአባላትን ገንዘብ የማስተዳደር ፣መምራት ፣ጥሪት ማፍራት፣መቆጠብና የመበደር አቅም እውቀትና ክህሎት በማዳበር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል ምክትል ኮሚሽነሩ።