* ከለውጡ ወዲህ በየትኛውም የክልሉ አካባቢ ለልማት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ያነሱ ሲሆን ለዚህም፡
* ከለውጡ ወዲህ በተሰራው ብርቱ ስራ ችግሮችን በመቀልበስ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በሌሎች ዘርፎች ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን፤
* የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና ሌሎች ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ሳይቆራረጡ በመገንባት ላይ መሆናቸውን፤
* ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተባብሮ ለመስራት የተጀመረው ጅማሮም ውጤት እያመጣ መሆኑን ፤
* ይህም ምቹ ሁኔታ ፓርቲዎች እውቀታቸውን እና ሌሎች አቅሞቻቸውን ለህዝብ ጥቅም እንዲያውሉ እድል መፍጠሩን፤
* በክልሉ አጋጥሞ የነበረው የፀጥታ ችግርም በቅንጅትና በትብብር መፍታት መቻሉን፤
* ይህንንም በዘላቂነት ለማስቀጠል የክልሉ መንግስትም ከፍተኛ በጀት፣ ሎጂስቲክስ እና የሰው ሃይል በመመደብ ዘላቂ የመልሶ ማቋቋም ስራ እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል ።
በዚህም የክልሉ ቁመና ከለውጡ ወዲህ እንደሀገር ስኬታማ ተግባራት ከተከናወነባቸውና እየተከናወነባቸው ከሚገኝባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች መካከል ይህ ክልል አንዱ እንደሆነም ጠቁመዋል።
በቀጣይም አሉ ርዕሰ መሰተዳድሩ
* በክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመው ለዚህም የሁሉንም ቀና ትብብር እንደሚያስፈልግ ፤
* በተለይም የኑሮ ውድነት መቀነስን ጨምሮ መሰረታዊ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ የክልሉ መንግስት በትኩረት ለመስራት በዕቅድ መያዙን፤
* የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ዳር ለማድረስ ክልሉ የሞት የሽረት ጉዳይ አድርጎ እንደሚሰራባቸው ጭምር ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ በነበራቸው የሚዲያ ቃለ መጠይቅ አንስተዋል ክልሉ ኮሙኒኬሽን በቴሌግራሙ ዘግቧል።