የአነስተኛ መድን ዋስትና ሽፋን የኅብረት ስራ ማህበራትን የአደጋ ስጋት ተጋላጭነት እንደሚቀንስ በኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን የፋይናንስ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ጠቆመ፡፡
አነስተኛ መድን ዋስትና ማለት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ስጋት (ጉዳት) ለመታደግ ተመጣጣኝ አረቦን በማስከፈል የሚያጋጥም ኪሳራን ለመከላከል ወይም ለመታደግ የሚያስችል አሰራር ነው፡፡
ዋስትናው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው በተለይም ከመደበኛ ኢንሹራንስ የተገለሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን አካታች በመሆኑ የመድን አባልነት ለኅብረት ስራ ማህበራትና አባላቶቻቸው ልዩ ጥቅም እንዳለው የአነስተኛ መድን ዋስትና ባለሙው አቶ ነጋሲ ስዩም ተናግረዋል፡፡ አባላት የብድር ዋስትና ተጠቃሚ በመሆናቸው ከስጋት ነፃ ያደርጋቸዋል ሲሉ ባለሙያው ጨምረው አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም የአነስተኛ መድና ዋስትና ተግባራዊ መደረጉ ተበዳሪው የወሰደውን የገንዘብ መጠን ሳይመልስ ብር የሞት አደጋ ቢያጋጥመው እዳው ወደ ቤተሰቦቹ እንዳይዞር ሙሉ በሙሉ በማህበሩ እንዲሸፈን የሚያደርግ በመሆኑ አባላትን ከስጋት ነፃ እያደረጋቸው መሆኑን የክልል ተሳታፊ ሰልጣኞች አስረድተዋል፡፡ በሀገር አቀፋ ደረጃ በቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተተገበረ ያለው ብድርን መሰረት ያደረገ አነስተኛ የመድን ዋስትና አገልግሎት በርካታ ስኬቶች እየተመዘገቡበት ነው፡፡
በመጨረሻም ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በሚኖርባት ሃገራችን ኢትዮጵያ ብድርን መሰረት ያደረገ አነስተኛ የህይወት መድን ዋስትና አገልፍሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ10 ፐርሰንት በታች መሆኑን በዘርፉ የተካሄዱ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ የኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ማህበራት ልማትና ዕድገት ሪፎርም የተፈለገውን ለውጥ እንዲያመጣ ከተፈለገ የአርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደርና የከተማ ነዋዎች የፋይናንስ አቅርቦት በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግና የአነስተኛ መድን ዋስትና ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ የአደጋ ተጋላጭነታቸውን መቀነስና መከላከል እንደሚገባ በኮሚሽኑ በተለያዬ ጊዜ የቀረቡ የጥናት ሰነዶች ይጠቁማሉ፡፡
ከኢፌዴሪ ህብረት ስራ ኮሚሽን የተወሰደ
All reactions:
1
2
Like
Comment
Mahajub Alhadi
መሬት የግለሰቦች መጠቀሚያ ሁነዋል!!