አሶሳ መጋቢት 13/2016 ዓ/ም።
አንድነት ኃላፊነቱ የተወሰነ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ዩኒየን ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ።
የውይይት መድረኩን ላይ ተገኝተው የክልሉ መሬትና ህብረት ስራ ማደራጃ ቢሮ የህብረት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑረዲን ሙክታር በክልሉ ዉስጥ የሚገኘዉን እምቅ አቅምና የተፈጠር ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም ህብረተሰቡን በህብረት ስራ ማህበራትና ዩኒየኖች በማደራጃ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተናግረዋል
የህብረተሰቡን የኢኮኖሚ አቅም ለማስደግ የተደራጁህብረት ስራ ማህበራትና ዩኒየኖችን ማጠናከር ወደ ስራ ማስገባት ብቸኛው አስፈላጊነት የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ኑረዲን ሙክታር አክለዉም አንድነት ኃላፊነቱ የተወሰነ የገዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ዩኒዬን ከጅምሩ ፈጣን ጥሩ የስራ እንቅስቃሴ እያደረገ ህብረት ስራ ማህበር ቢሆንም በሚጠበቀው ልክ ውጠታማ አለመሆኑን ገልጸው በልዩ ትኩረት ክትትል ድጋፍ በማድረግ የፋይናንስ ተደራሽነቱን እንዲያስፋፋ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
በዉይይቱ ወቅት ህብረት ስራ ማህበሩ በሚፈለገው አለማደግ ለዚህም:- የአባል አባላት ቁጥር አለመጨመሩን፣ የአባላት የቁጠባ ባህል በሚፈለገዉ ደረጃ እድገት እያሳየ አለመሆኑንና ተበዳሪዎች ብድር በወቅቱ ያለመመለሳቸውን ለገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ዩኒየኑ እድገት
መንሰኤ መሆናቸዉን የጠቀሱት ስሆን እነዚህን ችግሮች መፍታት በተላይም ብድር የማስመለስና ዩኒየኑን ማጠናከር ስራ እንዲሰራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
በዉይይት መድረኩ ላይ አሶሳ ዞን ግብርና መምሪያ፣ አሶሳ ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ፣ ኡራ እና አብራሞ ወረዳ ኃላፊዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
ዘገባዉ የቢሮው የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነዉ።