የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢኮኖሚ ክላስተር ሴክተር መስሪያ ቤቶቾ የብልጽግና ፓርቲ መሠረታዊ ድርጅት አመራሮችና አባላት ኮንፈረንስ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

(አሶሳ፣ መጋቢት 12/2016 ዓ/ም) “ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኢኮኖሚ ክላስተር ሴክተር መስሪያ ቤቶች የብልጽግና ፓርቲ የሁለት ዓመት ተኩል መሠረታዊ ድርጅት አመራሮችና አባላት ኮንፈረንስ በአሶሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በተመዘገቡ ስኬቶች እና ጉድለቶች ላይ በመምከር ለፓርቲው መጠናከር በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት የሚፈጠርም ይሆናል።
በኮንፈረንሱ ነጥረው የሚወጡ አቋሞችና አቅጣጫዎችን ማደራጀትና የቀጣይ ርብርብ ማዕከላትን ለይቶ ለተግባራዊነቱ የተሻለ መነሳሳት ለመፍጠርም ያለመ መድረክ እንደሆነም ተመላክቷል።
በመርሃ-ግብሩ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ይስሃቅ አብዱልቃድርን ጨምሮ የክላስተሩ አመራሮችና አባላት ተሳትፈዋል።
ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተወሰደ

Leave a Reply

Your email address will not be published.