‟ሙስና” የመኖርና ያለመኖር የህልዉና ጉዳይ ነዉ ተባለ፡፡
28/03/2013 ዓ.ም
የቤ/ጉ/ክ/መ/ የገጠርመሬት አስተዳደርና ኢንቨስትመንት ቢሮ እንዲሁም የአካ እና ደን ጥበቃ ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች በሙሉ በክልሉ ት/ቢሮ አዳራሽ በመገኘት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ17ኛ ጊዜ በኢትየጵያ ደረጃ ለ16ኛ ጊዜ‟ የትዉልድ ሥነ ምግባር ግንባታን በጠንካራ ዲስፕሊን በመምራት ሌብነትንና ብልሹ አሠራርን በመግታት የብልጽግና ጉዞአችንን እናፋጥናለን ” በሚል መርህ ቃል የሚከበረዉን ዓለም አቀፍ የጸረ- ሙስና ቀንን በማስመልከት ’በጋራ በፓናል ዉይይት አክብረዋል፡፡
በዚሁም መሠረት የአካ እና ደን ጥበቃ ባለስልጣን ኃላፊ የሆኑት አቶ አብዱልከሪም ሙሣ የፓናል ውይይቱን ሲከፍቱ እንደተናገሩት እኛ ማን ነን? በቀጣይስ በጸረ ሙስና ትግሉ ምን መሥራት አለብን? ብለን ራሳችንን መጠየቅና ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አስምረዉበታል፡፡
አቶ አበዱልከሪም ሙሣ በማስከተል ሀገራችንን ወደ ኋላ እንድትራመድና በድህነት አረንቋ ዉስጥ እንድትዘፈቅ ያደረጋት የሌብነት ጉዳይ መሆኑን ገልጸዉ ዜጋችን በጠንካራ ዲስፕሊን በመምራት ትዉልድን በመገንባት የብልጽግና ጉዞአችንን በማፋጠን ረገድ ጥረት መደረግ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
በመቀጠልም ስልጠናዉን የሰጡት የጸረ- ሙስና ኮሚሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ አወቀ ገ/መስቀል ሲሆኑ እርሳቸዉም የስለጠናዉን አበይት ዓላማ ያስረዱ ሲሆን፣ በየደረጃዉ ያሉ የአስፈጻሚና ፈጻሚ አካላት ከሙስናና ብልሹ አሰራር የጸዱ በማድረግ መነሳሳትን ለመፍጠር መሆኑን ገልጸዉ፣የሙስና ጉዳይ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ርብርብ በማድረግ የመደረክ አቢዮታዊ ከመሆን ይልቅ የተግባር ሰዉ በመሆን ሙስናንና ብልሹ አሰራርን የሚጠየፍ ትዉልድ መፍጠር ይኖርብናል በማለት ከተሳታፊዎች የተነሱትን አስተያየትና ጥያቄዎች ጠቅለል በማድረግ ምላሽ በመስጠት የፓናል ዉይይቱ ተጠናቋል፡፡