የገጠር መሬት አስተዳደደር እና ኢንቨስትመት ቢሮ የማናጅመንት አባላት፣ከፍተኛ ባለሙያዎች፤የፕሮጀክት ተጠሪዎች እና አስተባባሪዎች በበጀት ዓመቱ በ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም መስረት በዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮጀክት /RLLP/SLMP/ የተከናወኑ ስራዎችን በተመለከተ በባምባሲ ፤ ሆሞሻ እና አሶሳ ወረዳዎች ላይ በመገኘት ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እና የመስክ ጉብኝት አደረገ፡፡
**************************************************************************************************************************
በቀን 19.3.2013 ዓ.ም
የገጠር መሬት አስተዳደደርእና ኢንቨስትመት ቢሮ በባምባሲ ፤ ሆሞሻ እና አሶሳ ወረዳዎች ላይ የመስክ ጉብኙቱን እና ውይይቱን የመሩት የቢሮው ኃላፊ አቶ ገለታ ኃይሉ እንዳሉት የዚህ የመስክ ጉብኝት እና ውይይት ዋና ዓላማ የአንደኛውን ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም መሰረት በማድረግ በዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮጀክት እና በመደበኛ ስራ ላይ የተከናወኑት ተግባራት ምንም እንኳን የሚበረታቱ ተግባራት የተከናወኑባቸው ቢሆኑም ያሉትን ዉስንነቶችን በመለየት እና በጋራ መፍትሄ በማስቀመጥ በቀጣይ የተሻለ አፍጻጸም እንዲመዘገብ ማስቻል ሲሆን በአፈፃፀሞቹ ጉድለቶች ላይ የፅሁፍ ግብረ-መልስ ከመስጠት ይልቅ በግንባር በመገናኘት በዚህ በጀት ዓመት ብቻ ሳይወሰን ተንከባለው በመጡ በዕቅድ አፈፃፀም በቀጣይ ሊወሰዱ በሚገባቸው የመፍትሄ እርምጃዎች ላይ በመነጋገር ለቀጣይ ትግበራ ምቹ ሁኔታ መፍጠር በእጅጉ አስፈላጊ እንደሆነ የታመነበት ሲሆን የሚመለከታቸው የማናጅመንት አባላት፣ከፍተኛ ባለሙያዎች፤የፕሮጀክት ተጠሪዎች እና አስተባባሪዎች በተገኙበት ለመወያየት እና የተከናወኑ ስራዎችን ለማየት እንደሆ ገልጸዋል፡፡
በዚህም መሰረት በባምባሲ ወረዳ በዘላቂ መሬት አስተዳደደር ፕሮጀክት በ9 ቀበሌዎች ላይ 14‚500 ማሳዎችን በመለካት 12‚000 የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ለመስጠት ተችሏል፡፡ ፣በሆሞሻ ወረዳ በ4ቀበሌዎች ላይ 2‚‚912 ማሳዎችን በመለካት20‚18 የዞታ ማረጋገጫ ደብተር ለመስጠት እንደተቻለ ታውቋአልእንዲሁም በአሶሳ ወረዳ በ7ቀበሌዎች ላይ 16‚949 ማሳዎችን በመለካት11‚151የዞታ ማረጋገጫ ደብተር ለመስጠት እንደተቻለ ይታውቋአል፡፡
የስምሪት ቡድኑ በባምባሲ፤በሆሞሻ፤ኦዳ ቢልድግሉ፤አሶሳ ወረዳ እና ከአሶሳ ዞን በመገኘት ከሚመለከታቸው የወረዳ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር የጋራ ውይይት በማድረግ የሩብ ዓመቱን አፈጻጸም ግምገማ በማድረግ እና በስራ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት እና የቀጣይ ትግበራ መፍትሄ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
በመጨረሻም በባምባሲ ወረዳ መንደር አርባ አንድ/41/ ላይ በመገኘት በፕሮጀክቱ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በመውሰድ በአሳታፊ የገጠር መሬት አጠቃቀም ዕቅድ ላይ ያለውን አፈፃፀም በተመለከተ ከቀበሌ አመራሮች እና ከአርሶ አደሮች ጋር በመወያየትእና የመስክ ጉብኝት በማድረግ ተጠናቅቋል ፡፡