የGiZ-S2RAI Project ለገጠር መሬት ልኬትና ምዝገባ Project ሥራዎች አገልግሎት የሚዉሉ ሶስት TVS ሞተር ሳይክሎችን 253,565.22 ብር ግዢ በማድረግ ድጋፍ አደረገ፣
በቀን 2-4.2133ዓ.ም
የቤ/ጉ/ክ/መንግስት ገጠር መሬት አስተዳደርና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ገለታ ኃይሉ በተገኙበት የGiZ-S2RAI Project አስተባበሪ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ታደሠ ሶስት TVS ሞተር ሳይክሎችነ 253,565.22 ብር የተገዙ ሞተሮችን ቁልፍ አሰረክበዋል፡፡ እንደ አቶ ስንታየሁ ታደሠ ገለጻም የድጋፉ ዋና ዓላማም ለገጠር መሬት ልኬትና ምዝገባ ሥራዎች አገልግሎት የሚዉሉ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ፣በድጋፍ መልክ የተሰጡ ሞተሮችም ፕሮጀክቱ የገጠር መሬት ልኬትና ምዝገባ እየተካናወነ በሚገኝባቸዉ ለአሶሳ ወረዳ-1፣ ለባምባሲ ወረዳ-1 እና ለቢሮዉ-1 እንደሚሰጥ የቢሮዉ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ገለታ ኃይሉ የገለጹ ሲሆን፣ ለተደረገዉ ድጋፍ አመስግነዉ በቀጣይም የትብብር ሥራዎችን አጠናክረዉ በመቀጠል አርሶ አደሩን የመሬት ባለቤት ለማድረግ ትኩረት ተደረጎ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡